በዚያም ብዙዎች በእርሱ አመኑ።
በዚያም ስፍራ ብዙዎች በኢየሱስ አመኑ።
እዚያም ብዙ ሰዎች በእርሱ አመኑ።
በዚያም ብዙ ሰዎች አመኑበት።
ስለዚህ ወደ ማርያም ከመጡት፥ ኢየሱስም ያደረገውን ካዩት ከአይሁድ ብዙዎች በእርሱ አመኑ፤
ከዚህም ጋር ከአለቆች ደግሞ ብዙዎች በእርሱ አመኑ፤ ነገር ግን ከምኵራብ እንዳያስወጡአቸው በፈሪሳውያን ምክንያት አልመሰከሩለትም፤
በፋሲካ በዓልም በኢየሩሳሌም ሳሉ፥ ያደረገውን ምልክት ባዩ ጊዜ ብዙ ሰዎች በስሙ አመኑ፤
ሴቲቱም “ያደረግሁትን ሁሉ ነገረኝ፤” ብላ በመሰከረችው ቃል መሠረት፥ ከዚያች ከተማ፥ ብዙ የሰማርያ ሰዎች በእርሱ አመኑ።
በቃሉ ምክንያት ከፊተኞች ይልቅ ብዙ ሰዎች አመኑ፤
ከሕዝቡ ግን ብዙዎች አመኑበትና፥ “ክርስቶስ በመጣ ጊዜ ይህ ሰው ካደረጋቸው ምልክቶች የሚበልጥ ያደርጋልን?” አሉ።
ይህን ሲናገር ብዙዎች በእርሱ አመኑ።