የሚያዳምጠኝ ምነው በኖረልኝ! እነሆ የእጄ ምልክት፥ ሁሉን የሚችል አምላክ ይመልስልኝ፥ ከባላጋራዬ የተጻፈው የክስ ጽሑፍ ምነው በተገኘልኝ!
ኢዮብ 9:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የኃይል ነገር ከሆነ፥ ኃያሉ እርሱ እነሆ፥ የፍርድ ነገር ከሆነም፥ የችሎቱን ጊዜ ወሳኙ ማን ነው? ይላል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የኀይል ነገር ከተነሣ፣ እርሱ ኀያል ነው! የፍትሕም ነገር ከተነሣ፣ መጥሪያ ሊሰጠው የሚችል ማን ነው? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ባለኝ ኀይል ልታገለው እንዳልል፥ በኀይል እርሱን የሚቋቋም የለም፤ ተሟግቼ እረታዋለሁ እንዳልል፥ እርሱን ወደ ፍርድ ሸንጎ ሊያቀርበው የሚችል የለም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱ በኀይል ይይዛልና፤ ፍርዱን ማን ይቃወማል? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የኃይል ነገር ቢሆን እርሱ ኃያል ነው፥ የፍርድ ነገር ቢሆን፦ ጊዜን ወሳኙ ማን ነው? ይላል። |
የሚያዳምጠኝ ምነው በኖረልኝ! እነሆ የእጄ ምልክት፥ ሁሉን የሚችል አምላክ ይመልስልኝ፥ ከባላጋራዬ የተጻፈው የክስ ጽሑፍ ምነው በተገኘልኝ!