ልቡ እንደ ድንጋይ የደነደነ ነው፥ እንደ ወፍጮ ድንጋይ የጸና ነው።
እጅግ የተቀራረቡ ስለ ሆኑ፣ ነፋስ በመካከላቸው አያልፍም፤
አንዱ ከሌላው ጋር እጅግ የተጣበቀ በመሆኑ፥ በመካከላቸው ነፋስ እንኳ ማለፍ አይችልም።
በተመለሰም ጊዜ አራዊትና እንስሳ ይፈራሉ፥ በምድርም ላይ የሚንቀሳቀሱ ሁሉ ይሸበራሉ።
ሥጋውም እርስ በርስ የተጣበቀ ነው፥ ምንም ላያንቀሳቅሳቸው በእርሱ ላይ ጸንተዋል።
በተነሣ ጊዜ ኃያላን ይፈራሉ፥ ከድንጋጤም የተነሣ ይናወጣሉ።