ኢዮብ 39:20 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንደ አንበጣስ ታፈናጥረዋለህን? ግርማዊ ማንኰራፋቱ እጅግ ያስፈራል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንደ አንበጣ የምታስዘልለው አንተ ነህን? የማንኰራፋቱም ገናናነት አስፈሪ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንደ አንበጣ እየዘለሉ በማንኮራፋት ሰውን እንዲያስደነግጡ የምታደርጋቸው አንተ ነህን? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በፍጹም የጦር መሣሪያ አስጊጠኸዋልን? እምቢያውንስ በብርታት የከበረ አድርገኸዋልን? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንደ አንበጣስ አፈናጠርኸውን? የማንኰራፋቱ ክብር የሚያስፈራ ነው። |
“የፈረሶቻቸው ድምፅ ከዳን ተሰማ፤ ከአርበኞች ፈረሶች ማሽካካት የተነሣ ምድር ሁሉ ተንቀጠቀጠች፤ መጡም ምድሪቱንና በእርሷም ያለውን ሁሉ፥ ከተማይቱንና የተቀመጡባትንም በሉ።
በተራራ ላይ እንዳሉ ሰረገሎች ድምፅ፥ ገለባውንም እንደሚበላ እንደ እሳት ነበልባል ድምፅ፥ ለሰልፍም እንደ ተዘጋጀ እንደ ብርቱ ሕዝብ ያኰበኩባሉ።