ስለ እርሱ እግዚአብሔር የተናገረው ቃል ይህ ነው፦ የጽዮን ድንግል ትንቅሃለች፤ ታፌዝብሃለች፤ አንተ እየሸሸህ ሳለህ፥ የኢየሩሳሌም ልጃገረዶች ከኋላህ ሆነው ራሳቸውን ይነቀንቁብሃል።
ኢዮብ 39:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወደ ላይ ከፍ ከፍ ስትል በፈረስና በፈረሰኛው ትሳለቃለች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለመሸምጠጥም ክንፎቿን ስትዘረጋ፣ በፈረስና በጋላቢው ትሥቃለች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ተነሥታ በምትሮጥበት ጊዜ ግን፥ ፈረስና ፈረሰኛው ሊወዳደሩአት ቢሞክሩ ትስቅባቸዋለች። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዘመንዋ ወደ ላይ ራስዋን ከፍ ከፍ ታደርጋለች፥ በፈረሱና በፈረሰኛው ትሣለቃለች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወደ ላይ ከፍ ከፍ ስትል በፈረስና በፈረሰኛው ትሳለቃለች። |
ስለ እርሱ እግዚአብሔር የተናገረው ቃል ይህ ነው፦ የጽዮን ድንግል ትንቅሃለች፤ ታፌዝብሃለች፤ አንተ እየሸሸህ ሳለህ፥ የኢየሩሳሌም ልጃገረዶች ከኋላህ ሆነው ራሳቸውን ይነቀንቁብሃል።