እግዚእብሔርም ሁለት ታላላቆች ብርሃናትን አደረገ፥ ትልቁ ብርሃን በቀን እንዲሠለጥን፥ ትንሹም ብርሃን በሌሊት እንዲሰለጥን፥ ከዋክብትንም ደግሞ አደረገ።
ኢዮብ 38:33 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሰማይን ሥርዓት ታውቃለህን? በምድርስ ለይ እንዲፈጸም ማድረግ ትችላለህን? አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሰማያትን ሥርዐት ታውቃለህ? ይህንስ በምድር ላይ እንዲሠለጥን ማድረግ ትችላለህ? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሰማያት በምን ዐይነት ሥርዓት እንደሚተዳደሩ ታውቃለህን? ይህንንስ ደንብ በምድር ላይ እንዲሠራ ለማድረግ ትችላለህን? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሰማይን ሥርዐት፥ ከሰማይ በታችስ የሚሆነውን ታውቃለህን? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሰማይን ሥርዓት ታውቃለህን? በምድርስ ለይ እንዲሠለጥን ልታደርግ ትችላለህን? |
እግዚእብሔርም ሁለት ታላላቆች ብርሃናትን አደረገ፥ ትልቁ ብርሃን በቀን እንዲሠለጥን፥ ትንሹም ብርሃን በሌሊት እንዲሰለጥን፥ ከዋክብትንም ደግሞ አደረገ።