ኢዮብ 37:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በውኑ እግዚአብሔር እንዴት እንደሚያዝዛቸው፥ የደመናውንም ብርሃን እንዴት እንደሚያበራ አውቀሃልን? አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ደመናትን እንዴት እንደሚቈጣጠር፣ መብረቁንም እንዴት እንደሚያባርቅ ታውቃለህን? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ደመናን እንዴት እንደሚቈጣጠር፥ መብረቅንም እንዴት እንደሚያበርቅ ታውቃለህን? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔር ሥራውን እንዳከናወነ ከጨለማም ለይቶ ብርሃንን እንደ ፈጠረ እናውቃለን። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በውኑ እግዚአብሔር እንዴት እንደሚያዝዛቸው፥ የደመናውንም ብርሃን እንዴት እንደሚያበራ አውቀሃልን? |
ዓይናችሁን ወደ ላይ አንሥታችሁ ተመልከቱ፤ እነዚህን የፈጠረ ማን ነው? ሠራዊታቸውን በቍጥር የሚያወጣ እርሱ ነው፥ ሁሉንም በየስማቸው ይጠራቸዋል፤ በኃይሉ ብዛትና በክህሎቱ ብርታት አንድ እንኳ አይጎለውም።