ሰዎች ሁሉ ተመልክተውታል፥ ሰውም ከሩቅ ያየዋል።
ሰው ሁሉ አይቶታል፤ ሰዎችም በትኵረት ተመልክተውታል።
የእግዚአብሔርን ሥራ የሰው ዘር ሁሉ አይቶታል፤ ሰዎች በሩቅ ይመለከቱታል።
ሰው ሁሉ ራሱ፥ ኃጥኣን ሙታን እንደ ሆኑ ያስባል።
ይልቁንም ሰዎች የዘመሩለትን ሥራውን ማክበርን አስታውስ።
እነሆ፥ እግዚአብሔር ታላቅ ነው፥ እኛም አናውቀውም። የዘመኑም ቍጥር አይመረመርም።