ኢዮብ 35:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዐይኖችህን ወደ ሰማይ አቅንተህ እይ፥ ከአንተም በላይ ከፍ ያሉትን ደመናት ተመልከት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቀና ብለህ ወደ ሰማይ እይ፤ ከአንተ በላይ ከፍ ብለው ያሉትንም ደመናት ተመልከት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ቀና ብለህ ወደ ሰማይ ተመልከት፤ ከአንተ በላይ ከፍ ብሎ የሚታየውንም ደመና አስተውል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወደ ሰማይ ተመልከት፥ እይም፤ ደመናም ከአንተ በላይ ምን ያህል ከፍ እንዳለ ዕወቅ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዓይኖችህን ወደ ሰማይ አቅንተህ እይ፥ ከአንተም ከፍ ከፍ ያሉትን ደመናት ተመልከት። |
“በውኑ እግዚአብሔር በምድር ላይ ይኖራልን? እነሆ ሰማያት፥ ከሰማያትም በላይ ያለው ሰማይ ሊይዝህ አይችልም፤ እኔ የሠራሁት ይህ ቤተ መቅደስማ ምንኛ ያንስ!
ጌታ ለቁጣ የዘገየ፥ ኃይሉም ታላቅ ነው፥ በደለኛውንም፦ ንጹሕ ነህ አይልም፤ ጌታ መንገዱ በወጀብና በዐውሎ ነፋስ ውስጥ ነው፥ ደመናም የእግሩ ትቢያ ነው።
ጌታ ግን ሳሙኤልን፥ “መልኩን ወይም ቁመቱን አትይ፤ እኔ ንቄዋለሁና። ጌታ የሚያየው፥ ሰው እንደሚያየው አይደለም። ሰው የውጭውን ገጽታ ያያል፤ ጌታ ግን ልብን ያያል” አለው።