“ከዐይኖቼ ጋር ቃል ኪዳን ገብቻለሁ፥ እንግዲህ ቈንጆይቱን እንዴት በፍትወት እመለከታለሁ?
“ወደ ኰረዳዪቱ ላለመመልከት፣ ከዐይኔ ጋራ ቃል ኪዳን ገብቻለሁ።
“ቈንጆይቱን በፍትወት ዐይን እንዳልመለከት፥ ከዐይኔ ጋር ቃል ኪዳን ገብቼአለሁ።
“ከዐይኔ ጋር ቃል ኪዳን አደረግሁ፥ ድንግሊቱንም አልተመለከትሁም፤
ከዓይኔ ጋር ቃል ኪዳን ገባሁ፥ እንግዲህስ ቈንጆይቱን እንዴት እመለከታለሁ?
የእግዚአብሔር ልጆችም የሰውን ሴቶች ልጆች መልካሞች እንደ ሆኑ አዩ፥ ከመረጡአቸውም ሁሉ ሚስቶችን ለራሳቸው ወሰዱ።
“ልቤ ወደ ሌላይቱ ሴት ጐምጅቶ እንደሆነ፥ በባልንጀራዬም ደጅ አድብቼ እንደሆነ፥
ከንቱ ነገርን እንዳያዩ ዐይኖቼን መልስ፥ በመንገድህ ሕያው አድርገኝ።
ዐይኖችህ አቅንተው ይዩ፥ አተኩረው ፊት ለፊት ይመልከቱ።
ውበትዋን በልብህ አትመኘው፥ በዐይኖችዋም አትማረክ።
ምክንያቱም በዓለም ያለው ሁሉ፥ የሥጋ ምኞት፥ የዐይን ምኞት፥ በኑሮ ደረጃ መመካት፥ ከዓለም ነው እንጂ ከአብ አይደለም።