እግዚአብሔርም አለ፦ “እነሆ መብል ይሆናችሁ ዘንድ በምድር ፊት ሁሉ ላይ ዘሩ በእርሱ ያለውን ሐመልማል ሁሉ፥ የዛፍን ፍሬ የሚያፈራውንና ዘር ያለውንም ዛፍ ሁሉ ሰጠኋችሁ፥
ኢዮብ 28:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ምድር እንጀራን ታበቅላለች፥ ከበታቿ ያለው ግን እንደ እሳት ይገለባበጣል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከላይዋ ምግብን የምታስገኝ ምድር፣ ከታች በእሳት እንደሚሆን ትለዋወጣለች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ምድር ለምግብ የሚሆን እህል ታበቅላለች። ውስጥዋ በእሳት ቀልጦ ይገለባበጣል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንጀራ ከምድር ውስጥ ይወጣል፤ በእሳትም እንደሚሆን ታችኛው ይገለበጣል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንጀራ ከምድር ውስጥ ይወጣል፥ በእሳትም እንደሚሆን ታችኛው ይገለበጣል። |
እግዚአብሔርም አለ፦ “እነሆ መብል ይሆናችሁ ዘንድ በምድር ፊት ሁሉ ላይ ዘሩ በእርሱ ያለውን ሐመልማል ሁሉ፥ የዛፍን ፍሬ የሚያፈራውንና ዘር ያለውንም ዛፍ ሁሉ ሰጠኋችሁ፥