ኢዮብ 28:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለጨለማ ወሰን ይደረጋል፥ የጨለማውንና የሞት ጥላን ድንጋይ እስከ ጫፍ ድረስ ይፈላልጋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰው፣ እስከ ጨለማ መጨረሻ ይዘልቃል፤ ከድቅድቅ ጨለማ የማዕድን ድንጋይ ለማግኘት፣ እስከ ውስጠኛው ዋሻ ገብቶ ይፈልጋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሰዎች ጨለማን በማስወገድ እስከ መሬቱ ጥልቀት ዘልቀው በመግባት ራቅ ብሎ ወደሚገኘው ውስጥ በመግባት በድቅድቅ ጨለማው ውስጥ የማዕድን ድንጋይ ይፈልጋሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለጨለማ ወሰንን ያደርጋል፤ እርሱ ሁሉን ይመረምራል፥ የጨለማንና የሞት ጥላ ድንጋይንም ይመረምራል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሰው ለጨለማ ፍጻሜን ያደርጋል፥ የጨለማውንና የሞት ጥላን ድንጋይ እስከ ወሰኑ ድረስ ይፈላልጋል። |
ከሰማይም በታች የተደረገውን ሁሉ በጥበብ እፈልግና እመረምር ዘንድ ልቤን አተጋሁ፥ ይደክሙባት ዘንድ እግዚአብሔር ለሰው ልጆች የሰጣት ከባድ ጥረት ናት።