ኢዮብ 28:28 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሰውንም፦ ‘እነሆ፥ እግዚአብሔርን መፍራት ጥበብ ነው፥ ከክፋትም መራቅ ማስተዋል ነው’ አለው።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ሰውን፣ ‘እግዚአብሔርን መፍራት ጥበብ ነው፤ ከክፋትም መራቅ ማስተዋል ነው’ አለው።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “በዚያን ጊዜ ሰውን ‘እነሆ፥ ጥበብ ማለት እግዚአብሔርን መፍራት ነው፤ ማስተዋልም ማለት ከክፋት መራቅ ነው’ ብሎታል።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሰውንም፦ ‘እነሆ፥ እግዚአብሔርን መፍራት ጥበብ ነው፤ ከክፉ መራቅም ማስተዋል ነው’ ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሰውንም፦ እነሆ፥ እግዚአብሔርን መፍራት ጥበብ ነው፥ ከኃጢአትም መራቅ ማስተዋል ነው አለው። |
ጠብቁአት አድርጉአትም፥ ይህችን ሥርዓት ሁሉ ሰምተው፦ ‘በእውነት ይህ ታላቅ ሕዝብ ጠቢብና አስተዋይ ሕዝብ ነው’ በሚሉ በአሕዛብ ፊት ጥበባችሁና ማስተዋላችሁ ይህ ነውና።
ሆኖም የእግዚአብሔር ጠንካራ መሠረት የቆመው፦ “ጌታ የራሱ የሆኑትን ያውቃል፤” እንዲሁም “የጌታን ስም የሚጠራ ሁሉ ከዐመፅ ይራቅ፤” የሚለውን ማኅተም ታትሞ ነው።