ጥፋትና ሞት፦ ስለ እርሷ በወሬ ሰማን ብለዋል።”
ጥፋትና ሞት፣ ‘ወሬዋን ብቻ ሰማን’ ይላሉ።
ጥፋትና ሞት ‘ስለ እርስዋ የምናውቀው፥ በወሬ ብቻ ነው’ ይላሉ።
ሞትና ሲኦል ወሬዋን በጆሮቻችን ሰማን ብለዋል።
ጥፋትና ሞት፦ ወሬዋን በጆሮቻችን ሰማን ብለዋል።
ሲኦል በፊቱ ራቁትዋን ናት፥ ለጥፋትም መጋረጃ የለውም።
ቀላይ፦ በእኔ ውስጥ የለችም ይላል፥ ባሕርም፦ በእኔ ዘንድ የለችም ይላል።
ከሕያዋን ሁሉ ዐይን ተሰውራለች፥ ከሰማይ ወፎችም ተሸሽጋለች።
አሁንም ልጆቼ ሆይ፥ ስሙኝ፥ መንገዴንም የሚጠብቁ ምስጉኖች ናቸው።
ንጉሥም ነበራቸው፤ እርሱም የጥልቁ ጉድጓድ መልአክ ነው፤ ስሙም በዕብራይስጥ አባዶን በግሪክም አጶልዮን ነው።