ኢዮብ 28:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ብረት ከመሬት ውስጥ ይወሰዳል፥ ከቀለጠ ድንጋይም መዳብ ይወጣል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ብረት ከመሬት ውስጥ ይገኛል፤ መዳብም ከማዕድን ድንጋይ ቀልጦ ይወጣል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ብረት ከመሬት ይገኛል፤ መዳብም ከማዕድን ድንጋይ ቀልጦ ይወጣል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ብረትም ከመሬት ውስጥ ይወጣል፤ መዳብም እንደ ድንጋይ ይፈለጣል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ብረት ከመሬት ውስጥ ይወሰዳል፥ መዳብም ከድንጋይ ይቀለጣል። |
አሁንም፥ እነሆ፥ በድህነቴ ለጌታ ቤት መቶ ሺህ መክሊት ወርቅና አንድ ሚሊዮን መክሊት ብር፥ በሚዛንም የማይመዘን ብዙ ናስና ብረት አዘጋጀሁ፤ ደግሞም እንጨትና ድንጋዮች አዘጋጀሁ፥ አንተም በዚያ ላይ ጨምርበት።
ሳይጎድልህ እንጀራን ወደምትበላባት፥ አንዳችም ወደማታጣባት ምድር፥ ድንጋይዋ ብረት ወደ ሆነ፥ ከተራራዋም መዳብ ወደሚማስባት ምድር ያስገባሃል።