ኢዮብ 27:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኔ ስለ እግዚአብሔር ሥራዎች አስተምራችኋለሁ፥ ሁሉን በሚችል አምላክ ዘንድ ያለውን አልሸሽግም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ስለ እግዚአብሔር ክንድ አስተምራችኋለሁ፤ የሁሉን ቻዩንም አምላክ ዕቅድ አልሸሽግም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “የእግዚአብሔር ኀይል ምን ያኽል ታላቅ እንደ ሆነ አስተምራችኋለሁ፤ ሁሉን የሚችል አምላክ ያቀደውንም አልሸሽግባችሁም፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኔ ግን በእግዚአብሔር እጅ ምን እንዳለ አስተምራችኋለሁ፤ ሁሉን በሚችል አምላክ ዘንድ ያለውንም አልዋሽም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኔ ስለ እግዚአብሔር እጅ አስተምራችኋለሁ፥ ሁሉን በሚችል አምላክ ዘንድ ያለውን አልሸሽግም። |