ኢዮብ 24:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከተራሮች በሚወርድ ዝናብ ይረጥባሉ፥ መጠጊያም አጥተው ቋጥኙን ያቅፋሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከተራራ በሚወርድ ዝናብ በስብሰዋል፤ መጠለያ ዐጥተው ቋጥኝ ዐቅፈዋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በተራራ ላይ በሚዘንበው ዝናብ ሰውነታቸው ይረሰርሳል፤ መጠለያም አጥተው ቋጥኝ ተጠግተው ያድራሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በካፊያና ከተራሮች በሚወርድ ጠል ይረጥባሉ፤ መጠጊያም የላቸውምና ቋጥኙን ተተገኑ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከተራሮች በሚወርድ ዝናብ ይረጥባሉ፥ መጠጊያም አጥተው ቋጥኙን ያቅፋሉ። |
እኔ ተኝቻለሁ፥ ልቤ ግን ነቅቶአል፥ የውዴ ድምፅ ነው፥ እርሱም ያንኳኳል፥ እኅቴ፥ ወዳጄ፥ ርግቤ፥ የእኔ እንከን የለሽ፥ ራሴ በጠል፥ ጸጉሬም በሌሊት ነጠብጣብ ርሶአል።