ሕፃኖቻቸውን እንደ መንጋ ይለቃሉ፥ ልጆቻቸውም ይቧርቃሉ።
ልጆቻቸውን እንደ በግ መንጋ ያሰማራሉ፤ ሕፃናታቸውም ይቦርቃሉ።
እነርሱም እንደ በጎች ለዘለዓለም ይጠበቃሉ፤ ልጆቻቸውም በፊታቸው ይዘፍናሉ።
ሕፃናቶቻቸውን እንደ መንጋ ያወጣሉ፥ ልጆቻቸውም ይዘፍናሉ።
ኮርማቸው ይወልዳል፥ ዘሩንም አይጥለውም፥ ላማቸውም ትወልዳለች፥ አትጨነግፍም።
ከበሮና መሰንቆ ወስደው ይዘምራሉ፥ በእምቢልታ ድምፅ ደስ ይላቸዋል።
ችግረኛንም ከመከራው አወጣው፥ ቤተሰቦችን እንደ በጎች መንጋ አበዛ።