ኢዮብ 2:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታም ሰይጣንን፦ “ከወዴት መጣህ?” አለው። ሰይጣንም፦ “በምድር ላይ ዞርሁ፥ በእርሷም ተመላለስሁ” ብሎ ለጌታ መለሰ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ሰይጣንን፣ “ከወዴት መጣህ?” አለው። ሰይጣንም፣ “በምድር ሁሉ ዞርሁ፤ ወዲያና ወዲህም ተመላለስሁባት” ብሎ ለእግዚአብሔር መለሰ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔርም “ከወዴት መጣህ?” ብሎ ሰይጣንን ጠየቀው። ሰይጣንም “በምድር ዙሪያ ወዲያና ወዲህ እመላለስ ነበር” አለው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም ሰይጣንን፥ “ከወዴት መጣህ?” አለው። ሰይጣንም፥ “ከሰማይ በታች በምድር ላይ ዞርሁ፥ በእርስዋም ተመላለስሁ” ብሎ በእግዚአብሔር ፊት መለሰ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም ሰይጣንን፦ ከወዴት መጣህ? አለው። ሰይጣንም፦ በምድር ላይ ዞርሁ፥ በእርስዋም ተመላለስሁ ብሎ ለእግዚአብሔር መለሰ። |
ጌታም ሰይጣንን፦ “በውኑ አገልጋዬን ኢዮብን ተመለከትኸውን? በምድር ላይ እንደ እርሱ ፍጹምና ቅን፥ እግዚአብሔርንም የሚፈራ፥ ከክፋትም የራቀ ሰው የለም፥ ያለ ምክንያት ይጠፋ ዘንድ በእርሱ ላይ ብትገፋፋኝም እንኳን፥ እስከ አሁን ፍጹምነቱን ጠብቋል።”
እንደ እነርሱ ከሆነ የማያምኑ ሰዎችን ልቦና፥ የእግዚአብሔር ምሳሌ የሆነ የክርስቶስ የክብሩ ወንጌል ብርሃን እንዳያበራላቸው፥ የዚህ ዓለም አምላክ አሳውሯል።