ኢዮብ 19:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ወንድሞቼን ከእኔ ዘንድ አራቀ፥ የሚያውቁኝም አጥብቀው ተለዩኝ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ወንድሞቼን ከእኔ አርቋል፤ ከሚያውቁኝም ተገለልሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “እግዚአብሔር ወንድሞቼ ከእኔ እንዲርቁ አደረገ፤ የሚያውቁኝም ሰዎች ሁሉ ባይተዋር አደረጉኝ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ወንድሞች ተለዩኝ፥ ከእኔ ይልቅ ባዕዳንን ወደዱ። ጓደኞችም አላዘኑልኝም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወንድሞቼን ከእኔ ዘንድ አራቀ፥ የሚያውቁኝም አጥብቀው ተለዩኝ። |
ወንድሞቹና እኅቶቹ ቀድሞም ያውቁት የነበሩት ሁሉ ወደ እርሱ መጡ፥ በቤቱም ከእርሱ ጋር እንጀራ በሉ፥ ስለ እርሱም አዘኑለት፥ ጌታም ካመጣበት ክፉ ነገር ሁሉ አጽናኑት፥ እያንዳንዳቸውም ብርና የወርቅ ቀለበት ሰጡት።
ቤት። በሌሊት እጅግ ታላቅሳለች፥ እንባዋም በጉንጭዋ ላይ አለ፥ ከውሽሞችዋ ሁሉ የሚያጽናናት የለም፥ ወዳጆችዋ ሁሉ ወነጀሉአት ጠላቶችም ሆኑአት።