ኢዮብ 16:21 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሰው ልጅ ከባልንጀራው ጋር እንደሚምዋገት፥ ሰው በእግዚአብሔር ፊት ለመምዋገት ምነው በቻለ! አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰው ለወዳጁ እንደሚማልድ፣ በእግዚአብሔር ፊት የሚማልድ ሰው ምነው በተገኘ! አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሰውና ሰውን አወቃቅሶ የሚያስታርቅ እንዳለ ሁሉ፥ ምነው ሰውንና እግዚአብሔርን አወቃቅሶ የሚያስታርቅ በኖረ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጸሎቴ ወደ እግዚአብሔር ትድረስ፥ ዐይኔም በፊቱ እንባ ታፍስስ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሰው ልጅ ከባልንጀራው ጋር እንደሚምዋገት፥ ሰው በእግዚአብሔር ፊት ለመምዋገት ምነው በቻለ! |
የሚያዳምጠኝ ምነው በኖረልኝ! እነሆ የእጄ ምልክት፥ ሁሉን የሚችል አምላክ ይመልስልኝ፥ ከባላጋራዬ የተጻፈው የክስ ጽሑፍ ምነው በተገኘልኝ!
ከሠሪው ጋር ለሚታገል ወዮለት! በምድር ሸክላዎች መካከል ያለ ሸክላ ነው። ጭቃ ሠሪውን፦ ምን ትሠራለህ? ወይስ ሥራህ እጅ የለውም ይላልን?
ነገር ግን፥ ሰው ሆይ! ለእግዚአብሔር መልስ የምትሰጥ አንተ ማን ነህ? የተሠራ ነገር የሠራውን “ለምን እንዲህ አድርገህ ሠራኸኝ?” ይለዋልን?