ኢዮብ 14:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ዛፍ እንኳን ተሰፋ አለው፥ ቢቈረጥ የማቈጠቁጥ፥ ቅርንጫፉም የማደግ እድል አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ዛፍ እንኳ ቢቈረጥ፣ እንደ ገና ሊያቈጠቍጥ፣ አዳዲስ ቅርንጫፍም ሊያበቅል ተስፋ አለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ለተቈረጠ የዛፍ ጒቶ እንኳ ተስፋ አለው፤ እንደ ገና ሊያቈጠቊጥና ቅርንጫፎችም ሊያበቅል ይችላል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዛፍ ቢቈረጥ ደግሞ ያቈጠቍጥ ዘንድ፥ ተስፋ አለው፤ ቅርንጫፉም አያልቅም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዛፍ ቢቈረጥ ደግሞ ያቈጠቍጥ ዘንድ፥ ቅርንጫፉም እንዳያልቅ ተስፋ አለው። |
ከዐሥር አንድ ሰው እንኳን በምድሪቱ ቢቀር፤ እርሱም ደግሞ ይጠፋል፤ ነገር ግን የኮምበልና የባሉጥ ዛፍ በተቈረጠ ጊዜ ጉቶ እንደሚቀር፤ ቅዱሱም ዘር እንዲሁ በምድሪቱ ጉቶ ሆኖ ይቀራል።”