ከዚህም በኋላ ናቡዛርዳን በከተማይቱ ቀርተው የነበሩትንና ሌሎችን ሰዎች፥ እንዲሁም ከድተው ወደ ባቢሎናውያን የተጠጉትን ሁሉ ይዞ ወደ ባቢሎን አጋዛቸው፤
ኤርምያስ 52:30 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በናቡከደነፆር በሀያ ሦስተኛው ዓመት የዘበኞቹ አለቃ ናቡዘረዳን ከአይሁድ ሰባት መቶ አርባ አምስት ሰው ማርኮ አፈለሰ፤ በአጠቃላይ የሰዎቹ ብዛት አራት ሺህ ስድስት መቶ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ናቡከደነፆር በነገሠ በሃያ ሦስተኛው ዓመት፣ የክብር ዘበኞች አዛዥ ናቡዘረዳን፣ ሰባት መቶ አርባ ዐምስት አይሁድ ማርኮ ወስዷል። በአጠቃላይ አራት ሺሕ ስድስት መቶ ሰዎች ነበሩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንዲሁም በነገሠ በሃያ ሦስት ዓመቱ ሰባት መቶ አርባ አምስት አይሁድ በናቡዛርዳን እጅ ተማርከው ተወስደዋል፤ በጠቅላላው ተማርከው የተወሰዱት ሰዎች ቊጥር አራት ሺህ ስድስት መቶ ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በናቡከደነፆር በሃያ ሦስተኛው ዓመተ መንግሥት የአዛዦቹ አለቃ ናቡዛርዳን ከአይሁድ ሰባት መቶ አርባ አምስት ነፍስ ማርኮአል፤ ሰዎችም ሁሉ አራት ሺህ ስድስት መቶ ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በናቡከደነፆር በሀያ ሦስተኛው ዓመት የዘበኞቹ አለቃ ናቡዘረዳን ከአይሁድ ሰባት መቶ አርባ አምስት ነፍስ ማርኮአል፥ ሰዎች ሁሉ አራት ሺህ ስድስት መቶ ነበሩ። |
ከዚህም በኋላ ናቡዛርዳን በከተማይቱ ቀርተው የነበሩትንና ሌሎችን ሰዎች፥ እንዲሁም ከድተው ወደ ባቢሎናውያን የተጠጉትን ሁሉ ይዞ ወደ ባቢሎን አጋዛቸው፤
ናቡከደነፆር በባቢሎን በነገሠ በዐሥራ ዘጠነኛው ዓመት፥ አምስተኛው ወር በገባ በሰባተኛው ቀን ናቡዛርዳን ተብሎ የሚጠራው የናቡከደነፆር የክብሩ ዘበኞቹ አዛዥ ኢየሩሳሌም ገባ።
የዘበኞቹም አለቃ ናቡዘረዳን በከተማይቱ የቀሩትን ሕዝብ፥ ወደ እርሱም ኮብልለው የነበሩትን ሰዎች፥ የቀረውንም የሕዝቡን ቅሬታ ወደ ባቢሎን ማርኮ አፈለሳቸው።
የዘበኞቹም አለቃ ናቡዘረዳን የሕዝቡን ድኆች፥ በከተማይቱም ውስጥ የተረፈውን ሕዝብ፥ ሸሽተውም ወደ ባቢሎን ንጉሥ የተጠጉትን፥ የተረፉትንም የእጅ ሞያተኞች አፈለሰ።
የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ “ሰው ወይኑን እንደሚለቅም፥ እንዲሁ ከእስራኤል የተረፉትን ፈጽሞ ይለቅሙአችኋል፤ እጅህንም እንደ ለቃሚ በቅርንጫፎቹ ላይ ዳግመኛ ዘርጋ።”