La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኤርምያስ 52:25 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ከከተማይቱም በወታደሮች ላይ ተሾሞ ከነበረው አንዱን አዛዥ፥ በከተማይቱም ውስጥ ከተገኙት የንጉሡ አማካሪዎች ሰባቱን ሰዎች፥ የአገሩንም ሕዝብ ለጦርነት የሚመለምለውን የሠራዊቱን አለቃ ጸሐፊ፥ በከተማይቱም ከተገኙት ከአገሩ ሕዝብ ስልሳ ሰዎች ወሰደ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

በከተማው ውስጥ ከቀሩትም ሕዝብ፣ የተዋጊዎቹ ኀላፊ የነበረውን መኰንን፣ ሰባቱን የንጉሡን አማካሪዎች ከአገሬው ሕዝብ ወታደር የሚመለምለውን መኰንን ጸሓፊና በከተማው ውስጥ የተገኙትን ሌሎች ስድሳ ሰዎች ወሰደ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ከከተማይቱም የወታደሮች አዛዥ የሆነ አንድ ባለ ሥልጣንና እስከዚያ ጊዜ ድረስ በከተማይቱ ውስጥ የተገኙትን ሰባቱን የንጉሡን አማካሪዎች፥ የወታደራዊ ጉዳዮች ጸሐፊ የነበረውን የጦር አዛዡን ረዳትና ሌሎችንም ሥልሳ ታላላቅ ሰዎች ወሰደ፤

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ከከ​ተ​ማ​ዪ​ቱም በሰ​ል​ፈ​ኞች ላይ ተሾ​መው ከነ​በ​ሩት አን​ዱን ጃን​ደ​ረባ፥ በከ​ተ​ማ​ዪ​ቱም ከሚ​ገ​ኙት በን​ጉሡ ፊት ከሚ​ቆ​ሙት ሰባ​ቱን ሰዎች፥ የሀ​ገ​ሩን ሕዝብ የሚ​ያ​ሰ​ል​ፈ​ውን የሠ​ራ​ዊ​ቱን አለቃ ጸሐፊ፥ በከ​ተ​ማ​ዪ​ቱም ከተ​ገ​ኙት የሀ​ገሩ ሕዝብ ስድሳ ሰዎ​ችን ወሰደ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ከከተማይቱም በሰልፈኞች ላይ ተሾመው ከነበሩት አንዱን ጃንደረባ፥ በከተማይቱም ከሚገኙት በንጉሡ ፊት ከሚቆሙት ሰባቱን ሰዎች፥ የአገሩንም ሕዝብ የሚያሰልፈውን የሠራዊቱን አለቃ ጸሐፊ፥ በከተማይቱም ከተገኙት ከአገሩ ሕዝብ ስድሳ ሰዎች ወሰደ።

Ver Capítulo



ኤርምያስ 52:25
4 Referencias Cruzadas  

ከከተማይቱም የወታደሮች አዛዥ የሆነው አንድ ባለ ሥልጣን፥ እስከዚያ ጊዜ ድረስ በከተማይቱ የነበሩትን አምስቱን የንጉሥ አማካሪዎች፥ የአገሩን ሕዝብ ለወታደርነት ይመለምል የነበረውን መኰንንና ሌሎችንም ሥልሳ ሰዎችን ወሰደ፤


ባሮክም የኤርምያስን ቃላት በላይኛው አደባባይ በጌታ ቤት በአዲሱ በር መግቢያ ባለው በጸሐፊው በሳፋን ልጅ፥ በገማርያ ጓዳ በጌታ ቤት ውስጥ በሕዝቡ ሁሉ ጆሮ ከመጽሐፉ አነበበ።


“ከእነዚህ ታናናሾች አንዱን እንዳትንቁ ተጠንቀቁ፤ መላእክቶቻቸው በሰማያት ዘወትር በሰማያት ያለውን የአባቴን ፊት ያያሉ እላችኋለሁና።