ሀብታቸውን እንዲዘርፍ፤ ምርኮን እንዲያግበሰብስ፤ እንደ መንገድ ላይ ጭቃም እንዲረግጣቸው፤ አምላክ በሌለው ሕዝብ ላይ እልከዋለሁ፤ በሚያስቆጣኝም ሕዝብ ላይ እሰደዋለሁ።
ኤርምያስ 50:26 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከየአቅጣጫው በእርሷ ላይ ኑ፥ ጎተራዎችዋንም ክፈቱ፤ እንደ ተቈለለ ነዶ ከምርዋት ፈጽማችሁም አጥፉአት፥ ምንም ዓይነት ነገር አታስተርፉላት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከሩቅ መጥታችሁ በርሷ ላይ ውጡ፤ ጐተራዎቿን አፈራርሱ፤ እንደ እህል ክምር ከምሯት፤ ፈጽማችሁ አጥፏት፤ ምኗም አይቅር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከየአቅጣጫው ዝመቱባት፤ እህልዋ የተከማቸበትን ጐተራ ሁሉ ክፈቱ፤ ምርኮውንም እንደ እህል ምርት ቈልሉት፤ ምንም ነገር ሳትተዉ አገሪቱን አጥፉ! የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጊዜዋ ደርሶአልና ሣጥኖችዋን ከፍታችሁ እንደ ዋሻ በርብሯት፤ ጨርሳችሁም አጥፏት፥ ምንም አታስቀሩላት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከየበኩሉ በእርስዋ ላይ ውጡ፥ ጎተራዎችዋንም ክፈቱ፥ እንደ ክምርም አድርጓት ፈጽማችሁም አጥፉአት፥ አንዳችም አታስቀሩላት። |
ሀብታቸውን እንዲዘርፍ፤ ምርኮን እንዲያግበሰብስ፤ እንደ መንገድ ላይ ጭቃም እንዲረግጣቸው፤ አምላክ በሌለው ሕዝብ ላይ እልከዋለሁ፤ በሚያስቆጣኝም ሕዝብ ላይ እሰደዋለሁ።
በስምህም የምጠራህ የእስራኤል አምላክ ጌታ እኔ እንደሆንሁ ታውቅ ዘንድ በጨለማ የነበረችውን መዝገብ በስውርም የተደበቀችውን ሀብት እሰጥሃለሁ።
ከጌታ ቁጣ የተነሣ ባድማ ትሆናለች እንጂ ሰው አይቀመጥባትም፤ በባቢሎንም በኩል የሚያልፍ ሁሉ ይሣቀቃል በመጣባትም መቅሠፍት ሁሉ ያፍዋጫል።
የጌታ በቀል ነውና በዙሪያዋ ሆናችሁ በእርሷ ላይ ጩኹ፤ እጅዋን ሰጠች፤ ግንቦችዋ ወደቁ ቅጥሮችዋም ፈረሱ፤ እርሷን ተበቀሉ እንደ ሠራችውም ሥሩባት።
በባቢሎንም ውስጥ ቤልን እቀጣለሁ የዋጠውንም ከአፉ አስተፋዋለሁ፤ አሕዛብም ከዚያ ወዲያ ወደ እርሱ አይነጉዱም፥ የባቢሎንም ቅጥር ወድቆአል።
አንተም እንዲህ በል፦ ‘እኔ ከማመጣባት ክፉ ነገር የተነሣ እንዲሁ ባቢሎን ትሰጥማለች አትነሣምም።’ ” የኤርምያስ ቃላት እስከዚህ ድረስ ነው።
ወደ ሰማይ ወፎች ተመልከቱ፤ አይዘሩም፥ ወይም አያጭዱም፥ ወደ ጎተራም አይሰበስቡም፤ ነገር ግን የሰማዩ አባታችሁ ይመግባቸዋል፤ ታዲያ እናንተ ከእነርሱ እጅግ አትበልጡምን?
አሕዛብንም ይመታበት ዘንድ ስለታም ሰይፍ ከአፉ ይወጣል፤ እርሱም በብረት በትር ይገዛቸዋል፤ እርሱም ሁሉን የሚገዛ የእግዚአብሔርን የብርቱ ቁጣውን ወይን መጥመቂያ ይረግጣል።