ኤርምያስ 20:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እናቴ መቃብር እንድትሆነኝ ማኅፀንዋም ዘወትር ይዞኝ እንዲቆይ በማኅፀን ውስጥ አልገደለኝምና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እናቴ መቃብር ትሆነኝ ዘንድ፣ ማሕፀንም ሰፊ የዘላለም ማደሪያዬ እንዲሆን፣ ከማሕፀንም ሳልወጣ አልገደለኝምና። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም መቃብር እንድትሆነኝ ምነው በእናቴ ማሕፀን በገደለኝ ኖሮ! የእናቴ ማሕፀንም ለሁልጊዜ ትልቅ ሆኖ በኖረ ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እናቴ መቃብር ትሆነኝ ዘንድ፥ ማኅፀንዋም ዘወትር ይዞኝ ያቈይ ዘንድ በማኅፀን ውስጥ አልገደለኝምና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እናቴ መቃብር ትሆነኝ ዘንድ ማኅፀንዋም ዘወትር ይዞኝ ያቆይ ዘንድ በማኅፀን ውስጥ አልገደለኝምና። |
ሰው መቶ ልጆች ቢወልድ፥ እጅግ ዘመንም በሕይወት ቢኖር፥ ዕድሜውም እጅግ ዓመት ቢሆን፥ ነገር ግን ነፍሱ መልካምን ነገር ባትጠግብ፥ መቃብርንም ባያገኝ፥ ከእርሱ ይልቅ ጭንጋፍ ይሻላል አልሁ።
እናቴ ሆይ፥ ወዮልኝ! ለምድር ሁሉ የሙግትና የጥል ሰው የሆንሁትን ወለድሽኝ፤ ለማንም አላበደርሁም፥ ማንም ለእኔ አላበደረም፥ ነገር ግን ሁሉ ይረግመኛል።