ኤርምያስ 2:33 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ፍቅርን ለመሻት መንገድሽን እንዴት በጥንቃቄ ታስተካክያለሽ! ስለዚህም ለክፉዎች ሴቶች እንኳ መንገድሽን አስተምረሻል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ፍቅርን ለመፈለግ እንዴት ሥልጡን ነሽ? ልክስክስ ክፉ ሴቶች እንኳ ከመንገድሽ ብዙ ክፋት ይማራሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንቺ ፍቅረኞችሽን ተከትለሽ ለመሮጥ ምንኛ ብልኅ ሆንሽ? እጅግ ብልሹ የሆኑት ሴቶች እንኳ በአካሄድሽ ይመራሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ፍቅርን ለመሻት እንግዲህ በመንገድሽ የምትፈልጊው መልካም ምንድን ነው? እንዲህ አይደለም፤ መንገድሽን ታረክሺ ዘንድ ዳግመኛ በደልሽ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ፍቅርን ለመሻት መንገድሽን እንዴት ታቀኛለሽ! ስለዚህ ለክፉዎች ሴቶች እንኳ መንገድሽን አስተምረሻል። |
አንቺስ፦ ‘ራሴን አላረከስኩም በዓሊምንም አልተከተልኩም’ እንዴት ትያለሽ? በሸለቆ ያለውን መንገድሽን ተመልከቺ፥ ምን እንዳደረግሽም እወቂ፤ በመንገዶችዋ ላይ ወድያና ወዲህ የምትቅበዘበዥ ወጣት ግመል ሆነሻል፤
እነሆ እጄን በአንቺ ላይ ዘርግቻለሁ፥ ድርሻሽንም ቀንሻለሁ፥ ከክፉ መንገድሽ የተነሣ ለሚያፍሩ፥ ለጠላቶችሽ ለፍልስጥኤም ሴቶች ልጆች ፈቃድ አሳልፌ ሰጥቼሻለሁ።
አንቺ በእነርሱ መንገድ መሄድሽና ርኩሰታቸውንም መከተልሽ ብቻ ሳይሆን፥ በአጭር ጊዜ ውስጥ በመንገድሽ ሁሉ ከእነርሱ የበለጠ ምግባረ ብልሹ ነበርሽ።