Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




2 ዜና መዋዕል 33:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 ምናሴም ጌታ ከእስራኤል ልጆች ፊት ካጠፋቸው ከአሕዛብ ይልቅ ክፉ እንዲሠሩ በይሁዳና በኢየሩሳሌም የሚኖሩትን አሳተ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 ምናሴ ግን እግዚአብሔር በእስራኤላውያን ፊት ካጠፋቸው አሕዛብ የባሰ ክፉ ድርጊት ይፈጽሙ ዘንድ፣ የይሁዳንና የኢየሩሳሌምን ሕዝብ አሳተ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 ምናሴ የይሁዳንና የኢየሩሳሌምን ሕዝብ፥ የእስራኤል ልጆች ወደ ተስፋይቱ አገር በሚገቡበት ጊዜ፥ እግዚአብሔር ከፊታቸው እንዲባረሩ ያደረጋቸው ሕዝቦች ካደረጉት ይበልጥ የከፋ ኃጢአት እንዲሠሩ አደረጋቸው።”

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 ምና​ሴም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ፊት ካጠ​ፋ​ቸው ከአ​ሕ​ዛብ ይልቅ ክፉ ይሠሩ ዘንድ በይ​ሁ​ዳና በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም የሚ​ኖ​ሩ​ትን አሳተ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 ምናሴም እግዚአብሔር ከእስራኤል ልጆች ፊት ካጠፋቸው ከአሕዛብ ይልቅ ክፉ ይሠሩ ዘንድ በይሁዳና በኢየሩሳሌም የሚኖሩትን አሳተ።

Ver Capítulo Copiar




2 ዜና መዋዕል 33:9
18 Referencias Cruzadas  

ኢዮርብዓም ኃጢአት ስለሠራና የእስራኤልንም ሕዝብ ወደ ኃጢአት ስለ መራ፥ ጌታ እስራኤልን ይተዋል።”


ከእርሱም በፊት እንደነበረው እንደ አባቱ ኃጢአት በመሥራት የእስራኤልን ሕዝብ ወደ ኃጢአት መራ።


ምናሴ የይሁዳን ሕዝብ ወደ ጣዖት አምልኮና እግዚአብሔርን ወደሚያሳዝን ኃጢአት ከመምራት አልፎ፥ ንጹሓን የሆኑትን ብዙ ሰዎችን በመፍጀት የኢየሩሳሌምን መንገዶች በደም እንዲጥለቀለቁ አድርጎአል።


ነገር ግን ይህም ሁሉ ሆኖ ንጉሥ ምናሴ ባደረገው ክፉ ነገር ምክንያት በይሁዳ ላይ የነደደው አስፈሪ የእግዚአብሔር ቁጣ እስከ አሁን ድረስ ገና አልበረደም ነበር።


የይሁዳም ንጉሥ አካዝ ጌታን ክዷልና፥ ከእርሱም እጅግ ርቋልና ጌታ ስለ እርሱ ይሁዳን አዋረደው።


ጌታም ምናሴንና ሕዝቡን ተናገራቸው፤ ግን አልሰሙትም።


ጌታም ከእስራኤል ልጆች ፊት እንዳወጣቸው እንደ አሕዛብ ያለ ርኩሰት በጌታ ፊት ክፉ ነገር አደረገ።


እንዲሁም ጌታ ለዳዊትና ለልጁ ለሰለሞን፦ “እኔ ያዘዝኋቸውን ሁሉ፥ በሙሴም በኩል የተሰጠውን ሕግና ሥርዓት ፍርድንም ሁሉ ቢያደርጉ ቢጠብቁም፥ ለአባቶቻችሁ ከሰጠኋት ምድር እስራኤል እንደገና እንዲሰደዱ አላደርግም” ብሎ ነበር።


አስተዳዳሪ ለሐሰተኛ ነገር ትኩረት ቢሰጥ፥ ከእርሱ በታች ያሉት ሁሉ ዓመፀኞች ይሆናሉ።


ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ሁካታችሁ በዙሪያችሁ ካሉት አገሮች ይልቅ ሆኗል፥ በትእዛዜም አልሄዳችሁምና፥ ፍርዴንም አልጠበቃችሁምና፥ በዙሪያችሁም እንዳሉ እንደ አሕዛብ ፍርድ እንኳ አላደረጋችሁምና


“በእነዚህ ሁሉ ከፊታችሁ የማሳድዳቸው አሕዛብ ረክሰዋልና በእነዚህ ነገሮች ሁሉ ራሳችሁን አታርክሱ።


የዖምሪን ሥርዓትና የአክዓብን ቤት ሥራ ሁሉ ጠብቀሃልና፥ በምክራቸውም ሄዳችኋልና፤ ስለዚህ አንተን ለጥፋት ነዋሪዎቿን ደግሞ ለመዘባበቻ ሰጥቻችኋለሁ፥ የሕዝቤንም ስድብ ትሸከማላችሁ።


ታላቅና ብዙም ሕዝብ እንደ ዔናቅም ልጆች ቁመታቸው የረዘመ ነበሩ፥ ጌታ ከፊታቸው አጠፋቸው፥ እነርሱንም ቀምተዋቸው በስፍራቸው ተቀመጡ።


እኔም በዮርዳኖስ ማዶ ወደ ተቀመጡበት ወደ አሞራውያን ምድር አመጣኋችሁ፤ ከእናንተም ጋር ተዋጉ፥ አሳልፌም በእጃችሁ ሰጠኋችሁ፥ ምድራቸውንም ወረሳችሁ፤ ከፊታችሁም አጠፋኋቸው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos