ኤርምያስ 12:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ርስቴ በዱር እንዳለ አንበሳ ሆናብኛለች፤ ድምፅዋን በእኔ ላይ አንሥታለች፤ ስለዚህ ጠልቻታለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ርስቴ፣ በዱር እንዳለ አንበሳ ተነሥታብኛለች፤ በእኔም ላይ ጮኻብኛለች፤ ስለዚህ ጠላኋት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሕዝቤ በእኔ ላይ ተነሥተው እንደ ዱር አንበሳ ያገሡብኛል፤ ይህንንም አድራጎታቸውን እጠላለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ርስቴ በዱር እንደ አለ አንበሳ ሆናብኛለች፤ ድምፅዋንም አንሥታብኛለች፤ ስለዚህ ጠልቻታለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ርስቴ በዱር እንዳለ አንበሳ ሆናብኛለች፥ ድምፅዋን አንሥታብኛለች፥ ስለዚህ ጠልቻታለሁ። |
ክፋታቸው ሁሉ በጌልገላ አለ፤ በዚያ ሳሉ ጠላኋቸው፤ ስለ ሥራዎቻቸውም ክፋት ከቤቴ አስወጣቸዋለሁ፤ ከእንግዲህ ወዲያ አልወድዳቸውም፤ አለቆቻቸው ሁሉ ዓመፀኞች ናቸው።
ጌታ እግዚአብሔር፦ “የያዕቆብን ትዕቢት ተጸይፌአለሁ፥ የንጉሥ ቅጥሮቹንም ጠልቻለሁ፤ ስለዚህ ከተማይቱንና በውስጧ ያለውን ሁሉ አሳልፌ እሰጣለሁ” ብሎ በራሱ ምሎአል፥ ይላል ጌታ የሠራዊት አምላክ።
ነገር ግን ከቅርብ ጊዜ ጀምሮ ሕዝቤ እንደ ጠላት ሆኖ ተነሥቶአል፤ በሰላም ሳይፈሩ የሚያልፉትን ቀሚስንና መጐናጸፊያን ገፈፋችሁ፥ ከሰልፍ እንደሚመለሱ አደረጋችኋቸው።