እርሱም፦ “እኔ ከአንተ ጋር እሆናለሁ፤ እኔም እንደ ላክሁህ ምልክትህ ይህ ይሆናል፤ ሕዝቡን ከግብጽ ባወጣህ ጊዜ በዚህ ተራራ ላይ እግዚአብሔርን ታገለግላላችሁ” አለ።
ኤርምያስ 1:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኔ ላድንህ ከአንተ ጋር ነኝና በእነርሱ ምክንያት አትፍራ፥ ይላል ጌታ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም እኔ አድንህ ዘንድ ከአንተ ጋራ ነኝና አትፍራቸው” ይላል እግዚአብሔር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኔ ከአንተ ጋር ሆኜ ስለምታደግህ እነርሱን ከቶ አትፍራቸው፤ ይህን የተናገርኩ እኔ እግዚአብሔር ነኝ!” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኔ አድንህ ዘንድ ከአንተ ጋራ ነኝና ከፊታቸው የተነሣ አትፍራ” ይላል እግዚአብሔር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኔ አድንህ ዘንድ ከአንተ ጋር ነኝና ከፊታቸው አትፍራ፥ ይላል እግዚአብሔር። |
እርሱም፦ “እኔ ከአንተ ጋር እሆናለሁ፤ እኔም እንደ ላክሁህ ምልክትህ ይህ ይሆናል፤ ሕዝቡን ከግብጽ ባወጣህ ጊዜ በዚህ ተራራ ላይ እግዚአብሔርን ታገለግላላችሁ” አለ።
በውኃ ውስጥ ባለፍህ ጊዜ ከአንተ ጋር እሆናለሁ፥ በወንዞችም ውስጥ ባለፍህ ጊዜ አያሰምጡህም፤ በእሳትም ውስጥ በሄድህ ጊዜ አትቃጠልም፤ ነበልባሉም አይፈጅህም።
ጌታ ግን እንደ አስፈሪ ተዋጊ ከእኔ ጋር ነው፤ ስለዚህ አሳዳጆቼ ይሰናከላሉ አያሸንፉም፤ አይከናወንላቸውምና በጽኑ እፍረት ያፍራሉ፥ ለዘለዓለምም በማይረሳ ውርደት ይዋረዳሉ።
አንተን ለማዳን ከአንተ ጋር ነኝና፥ ይላል ጌታ፤ አንተንም የበተንሁባቸውን አሕዛብን ሁሉ ፈጽሜ አጠፋለሁ፥ አንተን ግን ፈጽሜ አላጠፋህም፤ እንደጥፋትህ መጠን እቀጣሃለሁ እንጂ ያለ ቅጣት ከቶ አልተውህም።
የኃጢአትንም ስርየት በእኔም በማመን በተቀደሱት መካከል ርስትን ያገኙ ዘንድ፥ ከጨለማ ወደ ብርሃን ከሰይጣንም ሥልጣን ወደ እግዚአብሔር ዘወር እንዲሉ ዐይናቸውን ትከፍት ዘንድ፥ ከሕዝቡና ወደ እነርሱ ከምልክህ ከአሕዛብ አድንሃለሁ።’
ጴጥሮስና ዮሐንስም በግልጥ እንደ ተናገሩ ባዩ ጊዜ፥ መጽሐፍን የማያውቁና ያልተማሩ ሰዎች እንደ ሆኑ አስተውለው አደነቁ፤ ከኢየሱስም ጋር እንደ ነበሩ አወቁአቸው፤
አሁንም፥ ጌታ ሆይ! ወደ ዛቻቸው ተመልከት፤ ለመፈወስም እጅህን ስትዘረጋ በቅዱስ ብላቴናህም በኢየሱስ ስም ምልክትና ድንቅ ሲደረግ፥ ባርያዎችህ በፍጹም ግልጥነት ቃልህን እንዲናገሩ ስጣቸው።”