ኢሳይያስ 7:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሶርያ ኤፍሬምና፤ የሮሜልዩ ልጅ ሊያጠፉህ እንዲህ ብለው ተማከሩ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሶርያ ኤፍሬምና፣ የሮሜልዩ ልጅ ሊያጠፉህ እንዲህ ብለው ተማከሩ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በእርግጥ ሶርያውያን ከእስራኤላውያንና ከንጉሣቸው ጋር ግብረ አበር በመሆን ሤራ አድርገዋል፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የአራም ልጅና የሮሜልዩ ልጅ ፋቁሔ፦ ክፉ ምክርን ተማከሩብህ እንዲህ ብለው፦ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሶርያና ኤፍሬም የሮሜልዩም ልጅ፦ ወደ ይሁዳ እንውጣ እናስጨንቀውም፥ እንስበረውም፥ የጣብኤልንም ልጅ እናንግሥበት ብለው ክፋት ስለ መከሩብህ፥ |
ለዳዊት ቤት፤ “ሶርያና ኤፍሬም ተባብረዋል” የሚል ወሬ በደረሰ ጊዜ፤ የዱር ዛፍ በነፋስ እንደሚናወጥ የአካዝና የሕዝቡ ልብ እንዲሁ ተናወጠ።