ኢሳይያስ 7:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚያን ቀን ጌታ ራቅ ካሉት ከግብጽ ወንዞች ዝንቦችን፤ ከአሦርም ምድር ንቦችን በፉጨት ይጠራል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚያ ቀን እግዚአብሔር ራቅ ካሉት ከግብጽ ወንዞች ዝንቦችን፣ ከአሦርም ምድር ንቦችን በፉጨት ይጠራል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ያም ዘመን በደረሰ ጊዜ ከዓባይ ወንዝ ዳርቻ ርቀት ግብጻውያን እንደ ዝንብ መንጋ፥ አሦራውያንም ከአገራቸው እንደ ንብ ሠራዊት እየተመሙ ይመጡ ዘንድ እግዚአብሔር ምልክት ይሰጣቸዋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚያም ቀን እንዲህ ይሆናል፤ እግዚአብሔር በግብፅ ወንዝ ዳርቻ ያለውን ዝንብ፥ በአሦርም ሀገር ያለውን ንብ በፉጨት ይጠራል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚያም ቀን እንዲህ ይሆናል፥ እግዚአብሔር በግብፅ ወንዝ ዳርቻ ያለውን ዝምብ በአሦርም አገር ያለውን ንብ በፉጨት ይጠራል። |
ስለ እርዳታ ወደ ግብጽ ለሚወርዱ በፈረሶችም ለሚደገፉ፥ ስለ ብዛታቸውም በሰረገሎች፥ እጅግ ብርቱዎችም ስለ ሆኑ በፈረሰኞች ለሚታመኑ፥ ወደ እስራኤልም ቅዱስ ለማይመለከቱ ጌታንም ለማይፈልጉ ወዮላቸው!
ኤፍሬም ከይሁዳ ከተለየበት ቀን ጀምሮ ታይቶ የማይታወቅ ዘመን በአንተ፤ በሕዝብህና በአባትህ ቤት ላይ ያመጣል፤ የሚያመጣውም የአሦርን ንጉሥ ነው።
በዚያም በተራራማው አገር ይኖሩ የነበር አሞራውያን ወጥተው ተጋጠሙአችሁ፥ እንደ ንብ መንጋ አሳደዱአችሁ፥ እስከ ሔርማም ድረስ በሴይር ድል ነሷችሁ።