ኢሳይያስ 63:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ቀሚስህ ስለምን ቀላ? ልብስህስ በወይን መጥመቂያ እንደሚረግጥ ሰው ልብስ ስለምን መሰለ?” አዲሱ መደበኛ ትርጒም መጐናጸፊያህ፣ ለምን በወይን መጭመቂያ፣ ወይን እንደሚረግጡ ሰዎች ልብስ ቀላ? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “የወይን ጠጅ ጨምቆ ለማውጣት የወይን ፍሬ ሲጨምቅ እንደ ነበረ ሰው ልብስህ ስለምን ቀይ ሆነ?” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ቀሚስህ ስለ ምን ቀላ? ልብስህስ በወይን መጭመቂያ እንደሚረግጥ ሰው ልብስ ስለ ምን መሰለ? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ቀሚስህ ስለ ምን ቀላ? ልብስህስ በወይን መጥመቂያ እንደሚረግጥ ሰው ልብስ ስለ ምን መሰለ? |
ይህ ከኤዶምያስ፥ ልብሱም የቀላ ከባሶራ የሚመጣ፥ አለባበሱ ያማረ፥ በጉልበቱ ጽናት የሚራመድ ማን ነው? “በጽድቅ የምናገር ለማዳንም የምበረታ እኔ ነኝ።”
አሕዛብንም ይመታበት ዘንድ ስለታም ሰይፍ ከአፉ ይወጣል፤ እርሱም በብረት በትር ይገዛቸዋል፤ እርሱም ሁሉን የሚገዛ የእግዚአብሔርን የብርቱ ቁጣውን ወይን መጥመቂያ ይረግጣል።