ኢሳይያስ 57:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከመዝጊያውና ከመቃኑ በኋላ መታሰቢያሽን አደረግሽ፤ እኔን ትተሽ ለሌላ ተገልጠሻል፥ ወጥተሽ መኝታሽን አስፍተሻል፤ ቃል ኪዳንም ተጋባሻቸው፥ ባየሽበትም ስፍራ ሁሉ መኝታቸውን ወደድሽ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከመዝጊያሽና ከመቃንሽ ጀርባ፣ የጣዖት ምስሎችሽን ሰቀልሽ፤ እኔን ትተሽ መኝታሽን ገላለጥሽ፤ በላይም ወጥተሽ በጣም ገለጥሽው፤ መኝታቸውን ከወደድሽላቸው ጋራ ስምምነት አደረግሽ፤ ዕርቃናቸውንም አየሽ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከበራችሁና ከመቃኖቹ በስተጀርባ የጣዖት ምስሎችን አስቀምጣችኋል፤ እኔን ትታችሁ ዝሙት ለመፈጸም ወደ አልጋዎቻችሁ ወጥታችኋል፤ በዝሙት ዋጋ ተደራድራችሁ ፍትወታችሁን ታረካላችሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከመዝጊያው በኋላ መታሰቢያሽን አደረግሽ፤ እኔን ብትተዪ የሚጠቅምሽ መሰለሽን? ከእኔም ይልቅ ከአንቺ ጋራ የሚተኙትን መረጥሽ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከመዝጊያውና ከመቃኑ በኋላ መታሰቢያሽን አደረግሽ፥ እኔን ትተሽ ለሌላ ተገልጠሻል፥ ወጥተሽ መኝታሽን አስፍተሻል፥ ቃል ኪዳንም ተጋባሻቸው፥ ባየሽበትም ስፍራ ሁሉ መኝታቸውን ወደድሽ። |