ኢሳይያስ 50:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነሆ፥ ጌታ እግዚአብሔር ይረዳኛል፤ ማን ይፈርድብኛል? እነሆ፥ ሁሉ እንደ ልብስ ያረጃሉ ብልም ይበላቸዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሚረዳኝ እርሱ ጌታ እግዚአብሔር ነው፤ የሚፈርድብኝስ ማን ነው? እነሆ፤ ሁሉም እንደ ልብስ ያረጃሉ፤ ብልም ይበላቸዋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሚረዳኝ ጌታ እግዚአብሔር ነው፤ ማን ይፈርድብኛል? ከሳሾቼ እንደ ልብስ ያረጃሉ፤ ብልም ይበላቸዋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነሆ፥ ጌታ እግዚአብሔር ይረዳኛል፤ ማን ይጎዳኛል? እነሆ፥ ሁላችሁ እንደ ልብስ ታረጃላችሁ፤ ብልም ይበላችኋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነሆ፥ ጌታ እግዚአብሔር ይረዳኛል፥ ማን ይፈርድብኛል? እነሆ፥ ሁሉ እንደ ልብስ ያረጃሉ ብልም ይበላቸዋል። |
በአንቺ ላይ የተሠራ መሣሪያ ሁሉ አይከናወንም፤ በፍርድም የሚነሣብሽን ምላስ ሁሉ ትፈርጂበታለሽ። የጌታ አገልጋዮች ርስት ይህ ነው፥ ጽድቃቸውም ከእኔ ዘንድ ነው፥ ይላል ጌታ።