ኢሳይያስ 45:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሁሉም ያፍራሉ ይዋረዱማል፥ ጣዖታትንም የሚሠሩ በአንድነት ወደ ውርደት ይሄዳሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የእጅ ጥበብ ባለሙያዎች ሁሉ ያፍራሉ፤ ይቀልላሉ፤ በአንድነት ይዋረዳሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጣዖቶችን የሚሠሩ ሁሉ ያፍራሉ፤ ይዋረዳሉ፤ ሁሉም በአንድነት ይዋረዳሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሚቃወሙት ሁሉም ያፍራሉ፤ ይዋረዱማል፤ አፍረውም ይሄዳሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሁሉም ያፍራሉ ይዋረዱማል፥ ጣዖታትንም የሚሠሩ በአንድነት ወደ ውርደት ይሄዳሉ። |
የተቀረጸውን ምስል የሚሠሩ ከንቱዎች ናቸው፤ የወደዱትም ነገር አይጠቅማቸውም፤ ምስክሮቻቸውም አያስተውሉም ደግሞ አያውቁም፥ ስለዚህ ያፍራሉ።
እናንተ ከአሕዛብ ወገን ሆናችሁ ያመለጣችሁ፥ ተሰብስባችሁ ኑ በአንድነትም ቅረቡ፤ የተቀረጸውን የምስላቸውን እንጨት የሚሸከሙና ያድን ዘንድ ወደማይችል አምላክ የሚጸልዩ እውቀት የላቸውም።