ኢሳይያስ 43:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዐይኖች ያሏቸውን ዕውር ሕዝቦችን፥ ጆሮዎችም ያሏቸውን ደንቆሮቹን አውጣ! አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዐይን እያላቸው የታወሩትን፣ ጆሮ እያላቸው የደነቈሩትን አውጣ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ዐይን እያላቸው የማያዩ ጆሮ እያላቸው የማይሰሙ፥ ሕዝቤን በአንድነት ሰብስቡ! የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዐይኖች እያሉአቸው የማያዩ ዕውሮችን ሕዝብ፥ ጆሮችም እያሉአቸው የማይሰሙ ደንቆሮዎችን አወጣሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዓይኖች ያሉአቸውን ዕውሮችን ሕዝብ፥ ጆሮዎችም ያሉአቸውን ደንቆሮቹን አውጣ። |
እርሱም እንዲህ አለኝ፤ “ወደዚህ ሕዝብ ሂድ፤ ‘መስማትን ትሰማላችሁ፤ ነገር ግን አታስተውሉም፤ ማየትንም ታያላችሁ፤ ነገር ግን ልብ አትሉም’ ብለህ ንገራቸው።
የሰው ልጅ ሆይ፥ በዓመፀኛ ቤት መካከል ተቀምጠሃል፥ እንዲያዩ ዐይን አላቸው ነገር ግን አያዩም፥ እንዲሰሙም ጆሮ አላቸው ነገር ግን አይሰሙም፥ እነርሱ ዓመፀኛ ቤት ናቸውና።