ኢሳይያስ 42:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኔ ጌታ ነኝ፤ ስሜ ይህ ነው፤ ክብሬን ለሌላ፥ ምስጋናዬንም ለተቀረጹ ምስሎች አልሰጥም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “እኔ እግዚአብሔር ነኝ፤ ስሜም ይህ ነው! ክብሬን ለሌላ፣ ምስጋናዬንም ለጣዖት አልሰጥም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ስሜ እግዚአብሔር ነው፤ የእኔንም ክብር የሚጋራ ሌላ አምላክ የለም፤ ጣዖቶችም ምስጋናዬን እንዲካፈሉ አልፈቅድም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኔ እግዚአብሔር አምላክህ ነኝ፤ ስሜ ይህ ነው፤ ክብሬን ለሌላ፥ ምስጋናዬንም ለተቀረጹ ምስሎች አልሰጥም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኔ እግዚአብሔር ነኝ፥ ስሜ ይህ ነው፥ ክብሬን ለሌላ፥ ምስጋናዬንም ለተቀረጹ ምስሎች አልሰጥም። |
ስለዚህ፥ አንተ፦ “ጣዖቴ ይህን አድርጎአል፥ የተቀረጸው ምስሌና ቀልጦ የተሠራው ምስሌ ይህን አዘዙኝ” እንዳትል፥ አስቀድሜ ነግሬህ ነበር፥ ከመሆኑም በፊት አሳይቼህ ነበር።
ሰምተሃል፤ አሁን ይህን ሁሉ ተመልከት፤ ይሄን ራስህ አትመሰክርም? የተሰወሩትን ያላወቅሃቸውንም አዲስ ነገሮችን ከአሁን ጀምሬ አሳይችኋለሁ።