ኢሳይያስ 41:25 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አንዱን ከሰሜን አነሣሁ መጥቶአልም፤ አንዱም ከፀሐይ መውጫ ስሜን የሚጠራ ይመጣል፤ በጭቃ ላይ እንደሚመጣ ሰው አፈርም እንደሚረግጥ ሸክለኛ በአለቆች ላይ ይመጣል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “አንዱን ከሰሜን አስነሣሁት፤ እርሱም ይመጣል፤ ከፀሓይ መውጫ የሚመጣው፣ ስሜን የሚጠራ ነው፤ ሸክላ ሠሪ ዐፈር እንደሚረግጥ፣ አለቆችን እንዲሁ እንደ ጭቃ ይረግጣል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “እኔ እግዚአብሔር አንድ መሪ ከሰሜን አስነሥቼአለሁ፤ መጥቶአልም። እርሱም ስሜን የሚጠራና ከፀሐይ መውጫ በኩል የሚመጣ ነው። ሸክላ ሠሪ የሸክላውን ዐፈር እንደሚረግጥ መሪዎችን ይረግጣል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከሰሜንና ከፀሐይ መውጫ የሚመጡትን አስነሣሁ፤ በስሜም ይጠራሉ፤ አለቆች ይምጡ፤ እንደ ሸክላ ሠሪ ጭቃና ጭቃን እንደሚረግጥ ሸክላ ሠሪ እንዲሁ ይረግጡአቸዋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አንዱን ከሰሜን አነሣሁ መጥቶአልም፥ አንዱም ከፀሐይ መውጫ ስሜን የሚጠራ ይመጣል፥ በጭቃ ላይ እንደሚመጣ ሰው አፈርም እንደሚረግጥ ሸክለኛ በአለቆች ላይ ይመጣል። |
ሀብታቸውን እንዲዘርፍ፤ ምርኮን እንዲያግበሰብስ፤ እንደ መንገድ ላይ ጭቃም እንዲረግጣቸው፤ አምላክ በሌለው ሕዝብ ላይ እልከዋለሁ፤ በሚያስቆጣኝም ሕዝብ ላይ እሰደዋለሁ።
ከምሥራቅ አንዱን ያስነሣ፥ በጽድቅም ወደ እግሩ የጠራው ማን ነው? አሕዛብንም አሳልፎ በፊቱ ሰጠው፥ ነገሥታትንም አስገዛለት፤ ለሰይፉ እንደ ትቢያ ለቀስቱም እንደ ተጠረገ እብቅ አድርጎ ሰጣቸው።
ቂሮስንም፦ “እርሱ እረኛዬ ነው”፤ እርሱም ኢየሩሳሌምን፦ “ትታነጺያለሽ ቤተ መቅደስም ይመሠረታል” ይላል፤ እኔም “ፈቃዴን ሁሉ ይፈጽማል” እላለሁ።
ጌታ ለቀባው፥ አሕዛብንም በፊቱ እንዲገዙለት፥ የነገሥታትንም ወገብ እዲፈታ፥ በሮቹም እንዳይዘጉ መዝጊያዎቹ በፊቱ እንዲከፈቱለት፥ ቀኝ እጁን ለያዘው ለቂሮስ እንዲህ ይላል፦
እኔ በጽድቅ አስነሥቼዋለሁ መንገዱንም ሁሉ አቀናለሁ፤ እርሱ ከተማዬን ይሠራል፥ በዋጋም ወይም በደመወዝ ሳይሆን ምርኮኞቼን ያወጣል፥ ይላል የሠራዊት ጌታ።
ሕዝብ ከሰሜን በእርሷ ላይ ወጥቶባታል ምድርዋንም ባድማ ያደርጋል፥ የሚቀመጥባትም አይገኝም፤ ከሰው ጀምሮ እስከ እንስሳ ድረስ ሸሽተው ሄደዋል።
በአንድ ላይም እንደ ጦረኞች ይሆናሉ፥ ጠላቶቻቸውንም በመንገድ ጭቃ ውስጥ የሚረግጡ ይሆናሉ፤ ጌታም ከእነርሱ ጋር ስለሆነ ጦርነት ይገጥማሉ፥ ፈረሰኞችንም ያሳፍራሉ።
ስድስተኛውም መልአክ ጽዋውን በታላቁ ወንዝ በኤፍራጥስ ላይ አፈሰሰ፤ ከፀሐይም መውጫ ለሚመጡ ነገሥታት መንገድ እንዲሰናዳላቸው ውሃው ደረቀ።