ኢሳይያስ 39:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱም፦ “በቤትህ ያዩት ምንድነው?” አለው፤ ሕዝቅያስም፦ “በቤቴ ያለውን ሁሉ አይተዋል፤ በቤተ መዛግብቴ ካለው ያላሳየኋቸው የለም” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነቢዩም፣ “በቤተ መንግሥትህ ያዩት ምንድን ነው?” አለው። ሕዝቅያስም፣ “በቤተ መንግሥቴ ያለውን ሁሉ አይተዋል፤ ከንብረቴ ያላሳየኋቸው ምንም ነገር የለም” አለ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢሳይያስም “በቤተ መንግሥቱ ምን አዩ?” ሲል ጠየቀው። ሕዝቅያስም “ሁሉን ነገር አይተዋል፤ በግምጃ ቤት ካለው ሀብት ሁሉ ለእነርሱ ያላሳየኋቸው ምንም ነገር የለም” አለው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኢሳይያስም፥ “በቤትህ ያዩት ምንድን ነው?” አለው፤ ሕዝቅያስም፥ “በቤቴ ያለውን ሁሉ አይተዋል፤ በቤቴ፥ እንዲሁም በቤተ መዛግብቴ ካለው ያላሳየኋቸው የለም” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱም፦ በቤትህ ያዩት ምንድር ነው? አለው፥ ሕዝቅያስም፦ በቤቴ ያለውን ሁሉ አይተዋል፥ በቤተ መዛግብቴ ካለው ያላሳየኋቸው የለም አለው። |
ነቢዩም ኢሳይያስ ወደ ንጉሡ ወደ ሕዝቅያስ መጥቶ፦ “እነዚህ ሰዎች ምን አሉ? ከወዴትስ መጡልህ?” አለው። ሕዝቅያስም፦ “ከሩቅ አገር ከባቢሎን መጡልኝ” አለው።
በሜዳ ያለው ተራራዬ ሆይ! ባለጠግነትህንና መዝገቦችህን ሁሉ የኮረብታውን መስገጃዎችህም ስለ ኃጢአት በድንበሮችህ ሁሉ ለብዝበዛ አሳልፌ እሰጣለሁ።
ኢያሱም አካንን እንዲህ አለው፦ “ልጄ ሆይ! ለእስራኤል አምላክ ለጌታ ክብር ስጥ፥ ለእርሱም ተናዘዝ፤ ያደረግኸውንም ንገረኝ፤ አትሸሽገኝ።”