በመጣበት መንገድ በዚያው ይመለሳል፤ ወደዚችም ከተማ አይመጣም፥ ይላል ጌታ።
በመጣበት መንገድ ይመለሳል፤ ወደዚህች ከተማም አይገባም” ይላል እግዚአብሔር።
ስለዚህም እርሱ ወደዚህች ከተማ ሳይገባ በመጣበት መንገድ ተመልሶ ይሄዳል፤ ይህን የተናገርኩ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።
በመጣበትም መንገድ በዚያ ይመለሳል፤ ወደዚህም ከተማ አይመጣም ይላል እግዚአብሔር፤
በመጣበት መንገድ በዚያው ይመለሳል፥ ወደዚችም ከተማ አይመጣም ይላል እግዚአብሔር።
ያለ ጌታ የሚሠምር፥ ጥበብም የለም፥ ማስተዋልም የለም፥ ምክርም የለም።
ከእንግዲህ ወዲህ ጨካኝን ሕዝብ፥ ቋንቋው ለማስተዋል የማይገባ የሆነውንና አንደበቱ ለማስተዋል ጸያፍ የሆነውን ሕዝብ አታይም።
ቁጣህና ትዕቢትህ ወደ ጆሮዬ ደርሶአል፤ ስለዚህ ስናጋዬን በአፍንጫህ ልጓሜንም በከንፈርህ አደርጋለሁ፤ በመጣህበትም መንገድ እመልስሃለሁ።
ስለ እኔም ስለ አገልጋዬም ዳዊት ይህችን ከተማ አድናታለሁ፥ እጋርዳታለሁም።”