ኢሳይያስ 33:24 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚያም የሚኖር ማንም፦ “ታምሜአለሁ” አይልም፤ በእርሷም ለሚኖሩ ሰዎች በደላቸው ይቅር ይባልላቸዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በጽዮን ተቀምጦ፣ “ታምሜአለሁ” የሚል አይኖርም፤ በዚያ የሚኖሩ ሰዎች ኀጢአትም ይቅር ይባላል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከጽዮን ነዋሪዎች መካከል “አመመኝ!” የሚል አይኖርም፤ በዚያም ለሚኖሩ ሁሉ የኃጢአት ይቅርታ ይደረግላቸዋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በውስጣቸውም የሚቀመጥ ሕዝብ፦ ደክሜአለሁ አይልም፥ በደላቸው ይቅር ይባልላቸዋልና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚያም የሚቀመጥ፦ ታምሜአለሁ አይልም፥ በእርስዋም ለሚቀመጡ ሰዎች በደላቸው ይቅር ይባልላቸዋል። |
እርሱም፦ “አንተ የጌታ አምላክህን ቃል ብትሰማ፥ በፊቱም ትክክል የሆነውን ብታደርግ፥ ትእዛዙንም ብታደምጥ፥ ሥርዓቱንም ሁሉ ብትጠብቅ፥ በግብፃውያን ላይ ያመጣሁትን በሽታ አላመጣብህም፤ ፈዋሽህ እኔ ጌታ ነኝና” አለ።
ጌታም የሕዝቡን ስብራት በጠገነ ዕለት፥ መቅሰፍቱ የቈሰለውንም በፈወሰ ዕለት፥ የጨረቃ ብርሃን እንደ ፀሐይ ብርሃን፥ የፀሐይም ብርሃን እንደ ሰባት ቀን ብርሃን ሰባት እጥፍ ይሆናል።
ለኢየሩሳሌም ልብ ተናገሩ፤ የተቀጠረችበት ወራት እንደ ተፈጸመ፥ ኃጢአትዋም እንደ ተሰረየ፥ ከጌታም እጅ ስለ ኃጢአትዋ ሁሉ ሁለት እጥፍ እንደ ተቀበለች ወደ እርሷ ጩኹ።
እንደትሩፍ የተውኳቸውን እነዚያን ይቅር እላቸዋለሁና በዚያን ወራት በዚያም ዘመን፥ ይላል ጌታ፥ የእስራኤል በደል የይሁዳም ኃጢአት ይፈለጋል ነገር ግን በዚያ ምንም አይገኝም።
ያደረግሽውን ሁሉ ይቅር ባልሁሽ ጊዜ፥ እንድታስቢውና እንድታፍሪ፥ ከውርደትሽም የተነሣ ደግሞ አፍሽን እንዳትከፍቺ ነው፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
በዚያም ቀን ከእነርሱ መካከል ደካማው እንደ ዳዊት እንዲሆን፥ የዳዊትም ቤት በፊታቸው እንደ እግዚአብሔር መልአክ እንደ ጌታ እንዲሆን፥ ጌታ በኢየሩሳሌም ለሚኖሩት መከታ ይሆናቸዋል።
ጌታም ሕማምን ሁሉ ከአንተ ያርቃል፥ የምታውቀውንም ክፉውን የግብጽ በሽታ ሁሉ በአንተ ላይ አያደርስብህም፥ በሚጠሉህ ሁሉ ላይ ግን ያመጣባቸዋል።
እንባዎችንም ሁሉ ከዐይኖቻቸው ላይ ይጠርጋል፤ ሞትም ከእንግዲህ ወዲህ አይሆንም፤ ኀዘንም ቢሆን ወይም ጩኸት ወይም ሥቃይ ከእንግዲህ ወዲህ አይሆንም፤ የቀደመው ሥርዓት አልፎአልና።”
በከተማው አደባባይዋም መካከል፥ በወንዙም ወዲያና ወዲህ፥ በየወሩ እያፈራ ዐሥራ ሁለት ፍሬ የሚሰጥ የሕይወት ዛፍ ነበረ፤ የዛፉም ቅጠሎች ለሕዝቦች መፈወሻ ነበሩ።