ኢሳይያስ 32:20 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እናንተ የበሬና የአህያ እግር እየነዳችሁ በውሃ ዳርቻ የምትዘዋወሩ ምን ያህል ትደሰቱ! አዲሱ መደበኛ ትርጒም በየወንዙ ዳር ዘር የምትዘሩ፣ በሬዎቻችሁንና አህዮቻችሁን በነጻነት የምታሰማሩ፣ ምንኛ ብፁዓን ናቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በየውሃው ምንጭ አጠገብ ዘራችሁን ስለምትዘሩና ለከብቶቻችሁና ለአህዮቻችሁ በቂ መሰማርያ ስለምታገኙ በበረከት የተሞላችሁ ትሆናላችሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ውኃ ባለበት፥ በሬና አህያም በሚረግጠው ቦታ የሚዘሩ ብፁዓን ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እናንተ የበሬና የአህያ እግር እየነዳችሁ በውሃ ሁሉ አጠገብ የምትዘሩ ብፁዓን ናችሁ። |