ኢሳይያስ 30:24 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መሬትንም የሚያርሱ በሬዎችና አህዮች በመንሽና በወንፊት የነጻውን ጨው ጨው የሚለውን ገፈራ ይበላሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የዕርሻ በሬዎችና አህዮች በመንሽና በላይዳ የተለየውን ገፈራና ድርቆሽ ይበላሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የምታርሱባቸው በሬዎችና አህዮች በጨው የታሸ መኖና በመንሽና በአካፋ ተገለባብጦ የጠራውን ገፈራ ይመገባሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መሬትንም የሚያርሱ በሬዎችና አህዮች በመንሽና በወንፊት የነጻውን ከገብስ ጋር የተቀላቀለውን ገፈራ ይበላሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) መሬትንም የሚያርሱ በሬዎችና አህዮች በመንሽና በወንፊት የነጻውን ጨው ጨው የሚለውን ገፈራ ይበላሉ። |
አንዳንዶቹን ሻለቆችና አምሳ አለቆች ያደርጋቸዋል፤ ሌሎቹን መሬቱን እንዲያርሱና እህሉን እንዲያጭዱ፥ ሌሎቹን ደግሞ የጦር መሣሪያና ለሠረገላ የሚሆኑትን ዕቃዎች እንዲሠሩ ያደርጋቸዋል።