ኢሳይያስ 3:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሰውም በአባቱ ቤት ከወንድሞቹ አንዱን ይዞ፤ “አንተ ልብስ ስላለህ መሪ ሁነን፤ ይህንንም የፍርስራሽ ክምር ግዛ” ይለዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰውም በአባቱ ቤት ከወንድሞቹ አንዱን ይዞ፣ “አንተ ልብስ ስላለህ መሪ ሁነን፤ ይህንም የፍርስራሽ ክምር ግዛ!” ይለዋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የቤተሰብ አባላት በአባታቸው ቤት አንዱን ወንድማቸውን መርጠው “አንተ ሌላው ቢቀር እንኳ የምትለብሰው ልብስ አለህ፤ ስለዚህ እባክህ አለቃችን ሁን፤ ፍርስራሽ ሁሉ በአንተ ሥልጣን ሥር ይሁን” ይሉታል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሰውም በአባቱ ቤተ ሰብእ ውስጥ ወንድሙን ይዞ፥ “አንተ ልብስ አለህ፥ አለቃም ሁንልን፥ ምግባችንም ከእጅህ በታች ትሁን” ቢለው፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሰውም በአባቱ ቤት ውስጥ ወንድሙን ይዞ፦ አንተ ልብስ አለህ አለቃም ሁንልን ይህችም ባድማ ከእጅህ በታች ትሁን ሲለው፥ |
በዚያን ቀን ሰባት ሴቶች አንዱን ወንድ ይዘው፤ “የራሳችንን ምግብ እንበላለን፤ የራሳችንንም ልብስ እንለብሳለን፤ በአንተ ስም ብቻ እንጠራና፤ ውርደታችንን አስቀርልን” ይሉታል።