እስራኤላውያን ይህን የፍርድ ውሳኔ በሰሙ ጊዜ ሰሎሞን የሕዝብ ጉዳዮችን በትክክለኛ ፍርድ የሚወስንበትን ጥበብ እግዚአብሔር የሰጠው መሆኑን ስለ ተገነዘቡ ታላቅ አክብሮት ሰጡት።
ኢሳይያስ 28:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በፍርድ ወንበር ላይ ለሚቀመጥም የፍርድ መንፈስ፥ ጦርንም ከከተማይቱ በር ላይ ለሚመልሱም ኃይል ይሆናል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱም በፍርድ ወንበር ላይ ለሚቀመጠው፣ የፍትሕ መንፈስ፣ ጦርን ከከተማዪቱ በር ላይ ለሚመልሱም፣ የኀይል ምንጭ ይሆናል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዳኝነት ለሚያገለግሉት የፍትሕ ጥበብ ይሰጣቸዋል፤ የከተማይቱን የቅጽር በሮች ከጠላት ለሚከላከሉትም ኀይልን ይሰጣቸዋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለፍርድና ከጥፋት ለሚያድናቸው ኀይል በፍርድ መንፈስ ይቀራሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በፍርድ ወንበር ላይ ለሚቀመጥም የፍርድ መንፈስ፥ ሰልፉን ወደ በር ለሚመልሱም ኃይል ይሆናል። |
እስራኤላውያን ይህን የፍርድ ውሳኔ በሰሙ ጊዜ ሰሎሞን የሕዝብ ጉዳዮችን በትክክለኛ ፍርድ የሚወስንበትን ጥበብ እግዚአብሔር የሰጠው መሆኑን ስለ ተገነዘቡ ታላቅ አክብሮት ሰጡት።
ከእርሱ ጋር ያለው ሥጋዊው ክንድ ነው፤ ከእኛ ጋር ያለው ግን የሚረዳንና የሚዋጋልን ጌታ አምላካችን ነው።” ሕዝቡም በይሁዳ ንጉሥ በሕዝቅያስ ቃላት ተበረታታ።
የጨካኞችም ቁጣ እስትንፋስ ቅጥርን እንደሚመታ ዐውሎ ነፋስ በሆነ ጊዜ፥ ለድሀው መጠጊያ፥ ለችግረኛው በጭንቁ ጊዜ መሸሸጊያ፥ ከውሽንፍር መጠለያ፥ ከሙቀትም ጥላ ሆነሃል።