ኢሳይያስ 28:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በባዕድ አፍ በልዩም ልሳን ለዚህ ሕዝብ ይናገራል፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንግዲያው እግዚአብሔር፣ በባዕድ ልሳን በእንግዳ ቋንቋ ለዚህ ሕዝብ ይናገራል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነሆ፥ እግዚአብሔር ይህንን ሕዝብ በአልተለመደ አነጋገርና በባዕድ ቋንቋ ይናገራል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በባዕድ አፍ በልዩም ልሳን ለዚህ ሕዝብ ይናገራል፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በባዕድ አፍ በልዩም ልሳን ለዚህ ሕዝብ ይናገራል፥ |
የእስራኤል ቤት ሆይ! እነሆ፥ ሕዝብን ከሩቅ አመጣባችኋለሁ፥ ይላል ጌታ፤ ጽኑ ጥንታዊ ሕዝብ ነው፥ ቋንቋቸውንም የማታውቀው የሚናገሩትንም የማታስተውለው ሕዝብ ነው።
“ቋንቋቸው እንግዳ በሆነ ሰዎች፥ በባዕዳንም አንደበት ለዚህ ሕዝብ እናገራለሁ፤ ይህም ሆኖ አይሰሙኝም፥ ይላል ጌታ” ተብሎ በኦሪትም ተጽፎአል።