ኢሳይያስ 27:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይህ ካልሆነ ግን ጉልበቴን ለእርዳታ ይያዝ፥ ከእኔ ጋር ሰላም ያድርግ፤ ከእኔ ጋር ሰላም ያድርግ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አለዚያ ይምጡና መሸሸጊያቸው ያድርጉኝ፤ ከእኔ ጋራ ሰላም ይፍጠሩ፤ አዎን፤ ከእኔ ጋራ ሰላም ያድርጉ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሆኖም የአትክልቱ ቦታ በእኔ ጥበቃ ከተማመነ እርሱ ወዳጄ ይሆናል፤ ከእኔም ጋር በሰላም ይኖራል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በውስጧ የሚኖሩ ይጮሃሉ፤ ከእርሱ ጋር ሰላምን እናድርግ፤ ከእርሱ ጋር ሰላምን እናድርግ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወይም ጕልበቴን ይያዝ፥ ከእኔ ጋር ሰላም ያድርግ፥ ከእኔ ጋር ሰላም ያድርግ። |
የጨካኞችም ቁጣ እስትንፋስ ቅጥርን እንደሚመታ ዐውሎ ነፋስ በሆነ ጊዜ፥ ለድሀው መጠጊያ፥ ለችግረኛው በጭንቁ ጊዜ መሸሸጊያ፥ ከውሽንፍር መጠለያ፥ ከሙቀትም ጥላ ሆነሃል።
ከአገልጋዬ በቀር ዕውር ማን ነው? እንደምልከው መልእክተኛዬስ ደንቆሮ የሆነ ማን ነው? እንደ ፍጹም ተገዢዬ ወይም እንደ ጌታ አገልጋይ ዕውር የሆነ ማን ነው?
ኢየሩሳሌም! ኢየሩሳሌም! ነቢያትን የምትገድል፥ ወደ እርሷ የተላኩትንም የምትወግር፥ ዶሮ ጫጩቶችዋን በክንፎችዋ በታች እንደምትሰበስብ ልጆችሽን ለመሰብሰብ ስንት ጊዜ ፈለግሁ፤ እናንተ ግን አልፈለጋችሁም።
ይሄውም እግዚአብሔር ሊዋሽ በማይቻል በሁለት በማይለወጥ ነገር፥ በፊታችን ያለውን ተስፋ ለመያዝ ለሸሸን ለእኛ ብርቱ መጽናናት እንዲሆንልን ነው።
የገባዖንም ሰዎች ኢያሱ ወደ ሰፈረበት ወደ ጌልገላ ልከው እንዲህ አሉት፦ “ባርያዎችህን ለመርዳት እጅህን አትመልስ፤ በተራራማው አገር የሚኖሩ የአሞራውያን ነገሥታት ሁሉ ተሰብስበውብናልና ፈጥነህ ወደ እኛ ውጣ አድነንም እርዳንም።”