የተማረከ ሁሉ ይወጋል፤ የተያዘም ሁሉ በሰይፍ ይወድቃል።
የተያዘም ሁሉ በሰይፍ ይገደላል።
የተበተኑት ሁሉ ይሞታሉ፤ የተሰበሰቡትም ሁሉ በጦር ይወድቃሉ።
የተገኘ ሁሉ የተወጋ ይሆናል፥ የተያዘም ሁሉ በሰይፍ ይወድቃል።
ከሰይፍ፥ ከተመዘዘው ሰይፍ፥ ከተለጠጠውም ቀስት ከጽኑም ሰልፍ ሸሽተዋልና።
የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር በከለዳውያን ምድር የሚፈጽመው ሥራ አለውና ጌታ የጦር ግምጃ ቤቱን ከፍቶ የቁጣውን የጦር መሣርያ አወጣ።
ወይፈኖችዋን ሁሉ እረዱ፥ ወደ መታረድም ይውረዱ፤ ቀናቸው፥ የመጐብኘታቸው ጊዜ ደርሶአልና ወዮላቸው!
በአንቺም ወንድንና ሴትን እሰባብራለሁ፤ በአንቺም ሽማግሌውንና ብላቴናውን እሰባብራለሁ፤ በአንቺም ጐልማሳውንና ድንግሊቱን እሰባብራለሁ፤