ሆሴዕ 6:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በእስራኤል ቤት የሚያስፈራን ነገር አይቻለሁ፤ በዚያ የኤፍሬም ዝሙት አለ፥ እስራኤልም ረክሶአል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በእስራኤል ቤት የሚሰቀጥጥ ነገር አይቻለሁ፤ በዚያ ኤፍሬም ዘማዊ ሆነ፤ እስራኤልም ረከሰ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እጅግ የሚያሠቅቅ ነገር በእስራኤል ሕዝብ ዘንድ አይቼአለሁ፤ ይኸውም ሕዝቡ ጣዖትን በማምለክ ዝሙት ረክሶአል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በእስራኤል ቤት የሚያሰፈራን ነገር አይቻለሁ፤ በዚያ የኤፍሬምንም ዝሙት አየሁ፤ እስራኤልም ረክሶአል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በእስራኤል ቤት የሚያስፈራን ነገር አይቻለሁ፥ በዚያ በኤፍሬም ውስጥ ግልሙትና ተገኘ፥ እስራኤልም ረክሶአል። |
ይህም የሆነበት ምክንያት ኢዮርብዓም ራሱ በሠራው ኃጢአትና የእስራኤልም ሕዝብ ኃጢአት እንዲሠሩ በማድረግ የእስራኤልን አምላክ የጌታን ቁጣ ስላነሣሣ ነው።
ይህም የሆነበት ምክንያት እስራኤላውያን በሠሩት ኃጢአት ከግብጽ ንጉሥ እጅ በመታደግ አውጥቶ ወደ ተስፋይቱ ምድር የመራቸውን አምላካቸውን እግዚአብሔርን በማሳዘናቸው ነበር፤ ይኸውም ለባዕዳን አማልክት ሰገዱ፤
“ስለዚህ ጌታ እንዲህ ይላል፦ በአሕዛብ መካከል፦ እንዲህ ያለ ነገር ማን ሰምቶአል? ብላችሁ ጠይቁ። የእስራኤል ድንግል በጣም የሚያስደነግጠውን ነገር አድርጋለች።
በኢየሩሳሌምም ነቢያት መካከል አስደንጋጭ ነገር አይቻለሁ፤ ያመነዝራሉ በሐሰትም ይሄዳሉ፤ ማንም ከክፋቱ እንዳይመለስ የክፉ አድራጊዎችን እጅ ያበረታሉ፤ ሁላቸውም እንደ ሰዶም የሚኖሩባትም እንደ ገሞራ ሆኑብኝ።
ጌታም በንጉሡ በኢዮስያስ ዘመን እንዲህ አለኝ፦ “ከዳተኛይቱ እስራኤል ያደረገችውን አየህን? ወደ ረዘመው ተራራ ሁሉ ከለመለመ ዛፍም ሁሉ በታች ሄደች በዚያም አመነዘረች።